Nhatty Man - ባዶ - Karaoke - ናቲ ማን -Bado - ማጀብያ ሙዚቃ እና ግጥም - New Ethiopian Music 2020



Published
https://www.instagram.com/nhatty_man
ቀኑ መሸ ጨላለመ
ብሎ ተስፋ ቆርጦ ከደከመ
ደስታውን ያራቀው ለታ
ያኔ ነው ሰው የሚረታ

በእድሜዬ አላየው
ሐሳብን ትቶ ሁሉን ኣሳክቶ ውጥኑ ሰምሮ የኖረ ሰው
በእድሜዬ አላየው
ሐሳብን ትቶ ሁሉን ኣሳክቶ ውጥኑ ሰምሮ የኖረ ሰው

በእኛ አልተጀመረም ባንቺ ባንተ ወይም በእኔ
ህይወት ጠአመ ሁለት ፈሳሽ ወራጅ ሁሌ
ቀና በይ ቀና በል ቀና ያለ ቀን ያልፋል
ፅኑ ልብ ፋና ነው ድቅድቁን ይገፋል

እኛ ከሌለን ባዶ
አዎ ሁሉ ባዶ

ዋናው ዋናው ዋናው (ዋናው)
ዋናው ዋናው ዋናው (ዋናው)

ዋናው ነገር ጤና መቆየት ነው ደጉ
ባለው ወይም ባጣው ሰው አይደል መአረጉ
ዋናው ነገር ሰላም የልብ ሙሉነት
የሚያልፍ ቀን አይነግር የሰውን ማንነት

ዋናው ነገር ጤና መቆየት ነው ደጉ
ባለው ወይም ባጣው ሰው አይደል መአረጉ
ዋናው ነገር ሰላም የልብ ሙሉነት
የሚያልፍ ቀን አይነግር የሰውን ማንነት

ዋናው ዋናው ዋናው
እኛ ከሌለን ባዶ
አዎ ሁሉ ባዶ