Nhatty Man -እመነኝ - Karaoke ናቲ ማን -Emenegne- ማጀብያ ሙዚቃ እና ግጥም



Published
#እመነኝ
www,nhattyma.com
እመነኝ እመነኝ
እመነኝ እመነኝ
እመነኝ እመነኝ

እስኪ ና ቁጭ በል እህ በል አድምጠኝ የሆዴን
አረፍ በል ከጥላው ከዋርካው
ላንተ የኔን ኑሮ መጠኑን ሚዛኑን
ምን ይሆን መለኪያው
እስኪ ና ዝቅ በል ውረድ ወደ መሬት
ውረድ ወደ መሬት እመሬት
አይተህ ብትረዳው አይንህ ቢመለከት
የእኛን ኑሮ የእኛን ህይወት
የእናንተ ቁም ነገር የእናንት ክርክር
ጥማድ ለእኔ አይገዛ አያድስም ሞፈር
ሚታይ ሚናፈሰው በየሞገዱ ላይ
ቅንጣት ደስታን እንጂ የእኛን ችግር አያይ

እመነኝ እመነኝ
እመነኝ እመነኝ
እመነኝ እመነኝ

እስኪ ና ዝቅ በል ግልጽ አንነጋገር የእውነት በል እንወቃቀስ ስለፍቅር
ስንት አለ በሆዴ እህ ብዬፍርዱን ለሱ ትቼ ያለፍኩት ሳልናገር
እስኪ ና ዝቅ በል ውረድ ወደ መሬት
ውረድ ወደ መሬት እመሬት
አይተህ ብትረዳው አይንህ ቢመለከት
የእኛን ኑሮ የእኛን ህይወት
የእናንተ ቁም ነገር የእናንት ክርክር
ጥማድ ለእኔ አይገዛ አያድስም ሞፈር
ሚታይ ሚናፈሰው በየሞገዱ ላይ
ቅንጣት ደስታን እንጂ የእኛን ችግር አያይ

እመነኝ እመነኝ
እመነኝ እመነኝ
እመነኝ እመነኝ

እፍኝ ሳይዘራ ግፍ ሳይፈራ
ስንት አለ ያጨደ የሞላ ጎተራ
የሞላ ጎተራ
አንተም ጥበበኛው 3X
አንተም ባለዝናው
በባህሌ ደምቀህ
በባህሌ ኮርተህ
በባህሌ ደምቀህ አጊጠህ በዜማው
የውስጤን ትኩሳት ምነው የማታወራው
ከአንድ እናት ተፈጥረን
ከአንድ እናት ተፈጥረን ሆነን በአንድ ላይ
ኑሮአችን ለየቅል ምድር እና ሰማይ 4X
እፍኝ ሳይዘራ ግፍ ሳይፈራ
ስንት አለ ያጨደ የሞላ ጎተራ