Nhatty Man - ሸብ አድርጎ Karaoke ናቲ ማን- Sheb Adrgo - ማጀብያ ሙዚቃ እና ግጥም



Published
#ሸብአድርጎ
www,nhattyman.com
አለኝ ጉዳይ
አለኝ ጉዳይ
አለኝ ጉዳይ
ሀገሬ ላይ

እግሩ እንደመራው በፊናው ወቶ
ባላሰበበት ቢከርም እርቆ
ሁሉን ባለበት በቸር ያቆየው
ቀን እንደገፋው ቀን እስኪዳኘው
ዘሎ ቦርቆ በምድርሽ ላይ
የልጅ መልኩ ወዝቶ
በአፈርሽ ሲሳይ
ማንስ ጨክኖ
ፊቱን ባንቺ ያዞራል
እንዴትስ ብሎ ሀገሩን ይጠላል
ያላለቀ ያልተቋጨ ሁሉ አለው ጉዳይ
ሀገሩ ላይ
ያላለቀ ያልተቋጨ ሁሉ አለው ጉዳይ
ኢትዮጵያ ላይ

ሸብ አርጎ
በፍቅር አስሮ
አንድ አድርጎሰብስቦ ልጆችሽን
የዓለም ያርገው ደስታሽን
ሸብ አርጎ
በፍቅር አስሮ
አንድ አድርጎሰብስቦ ልጆችሽን
የዓለም ያርገው ደስታሽን

ኑሮ ቢሞላ ወይም ቢጎድል
ለሀዘን ለደስታው ማን ያንችን ሊያህል
ዘመን ግርማሽን ቢያደበዝዘው
ቤት አለኝ ማለት እሱም ኩራት ነው
ገመናሽ ቢወራ አልፎ ከማጀትሽ
አንገቴን አልደፋም ትልቅ ነው ታሪክሽ

ያላለቀ ያልተቋጨ ሁሉ አለው ጉዳይ
ሀገሩ ላይ
ያላለቀ ያልተቋጨ ሁሉ አለው ጉዳይ
ኢትዮጵያ ላይ

ሸብ አርጎ
በፍቅር አስሮ
አንድ አድርጎ
ሰብስቦ ልጆችሽን
የዓለም ያርገው ደስታሽን
ሸብ አርጎ
በፍቅር አስሮ
አንድ አድርጎ
ሰብስቦ ልጆችሽን
የዓለም ያርገው ደስታሽን

ያላለቀ ያልተቋጨ ሁሉ አለው ጉዳይ
ሀገሩ ላይ
ያላለቀ ያልተቋጨ ሁሉ አለው ጉዳይ
ኢትዮጵያ ላይ

ሸብ አርጎ
በፍቅር አስሮ
አንድ አድርጎ
ሰብስቦ ልጆችሽን
የዓለም ያርገው ደስታሽን
ሸብ አርጎ
በፍቅር አስሮ
አንድ አድርጎ
ሰብስቦ ልጆችሽን
የዓለም ያርገው ደስታሽን

ሸብ አርጎ
ይሄ ነው ምኞቴ
አንድ አድርጎ
ናፍቆት ፍላጎቴ
ልጆችሽን
በህይወት እያለው በእድሜ በዘመኔ
ደስታሽን
እንዳየው ባይኔ

ሸብ አርጎ
ይሄ ነው ምኞቴ
አንድ አድርጎ
ናፍቆት ፍላጎቴ
ልጆችሽን
በህይወት እያለው በእድሜ በዘመኔ
ደስታሽን
እንዳየው ባይኔ

ይሄ ነው ምኞቴ
ናፍቆት ፍላጎቴ
በህይወት እያለው በእድሜ በዘመኔ
እንዳየው ባይኔ
ይሄ ነው ምኞቴ
ናፍቆት ፍላጎቴ
በህይወት እያለው በእድሜ በዘመኔ
እንዳየው ባይኔ
ይሄ ነው ምኞቴ
ናፍቆት ፍላጎቴ
በህይወት እያለው በእድሜ በዘመኔ
እንዳየው ባይኔ
ይሄ ነው ምኞቴ
ናፍቆት ፍላጎቴ
በህይወት እያለው በእድሜ በዘመኔ
እንዳየው ባይኔ