Error inserting record: Duplicate entry '216.73.216.60-2025-10-25 00:34:47' for key 'ip_address_date_index' Nhatty Man - ይቆማል ወይ - Karaoke ናቲ ማን - Yikomal Woy - ማጀብያ ሙዚቃ እና ግጥም - New Ethiopian Music 2020

Nhatty Man - ይቆማል ወይ - Karaoke ናቲ ማን - Yikomal Woy - ማጀብያ ሙዚቃ እና ግጥም - New Ethiopian Music 2020



Published
#ይቆማል ወይ
Subscribe for more ...
https://www.instagram.com/nhatty_man/?hl=en
https://www.facebook.com/realNhattyman/
https://www.nhattyman.com
ይቆማል ወይ
ህይወት ይቆማል ወይ
አጣህ ቸገረህ ብሎ ዞር ብሎ ያላየህ
ከፊት ይገኛል ቀድሞ ሊኮንን ሊወቅስህ
ያለስምህ ስም ሊሰጥህ
እንዴት ነው ብሎ በድካምህ ያላየህ
ከፊትህ ይገኛል ሊኮንን ሊወቅስህ
ያለ ስም ስም ሊሰጥህ

ስቀህ እለፍ እንጂ አትቁም ከቶ
ከህሊና በላይ ለራስ ዳኛ ከየት መቶ
አንተው ስታውቀው የእውነት ውስጥህን
በሰው አሉባልታ አጣጥቁር ልብህን
ይቆማል ወይ ይቆማል ወይ
ምን ተባለ ብሎ ህይወት ይቆማል ወይ
ይቆማል ወይ ይቆማል ወይ
ሰው አለ ብሎ ህይወት ይቆማል ወይ
ይቆማል ወይ ይቆማል ወይ
ምን ተባለ ብሎ ህይወት ይቆማል ወይ
ንገሩኝ

ልፋት ድካምሽንም ሽሮ
ስም ቢያወጣልሽ ሀገር ቀድሞ
አንቺ ታውቂያለሽ ንጹነትሽን
ሁሉን በጽናት ማለፍሽን
ያኔ ያልነበረ ፊት ጨርሶ
ከሳሽ ፈራጅ ነኝ ባዩ ደርሶ
እንዳይፈትነው ጽናትሽን
እንዳያጠቁረው ልብሽን

ድንቅ ሀሳቡን ይዞ ሳያበጀው
የአሉባልታ ሰደድ እየፈጀው
ስንቱ ተመለሰ ከአለመበት
በኮናኝ አንደበት

እንቅልፍ አቶ ኖረ ከሃሳብ ጋር
በሰው አፍ መዋልን እየፈራ
ስንቱ ተመለሰ ከአለመበት
በኮናኝ አንደበት

ይቆማል ወይ ይቆማል ወይ
ሰው አለ ብሎ ህይወት ይቆማል ወይ
ይቆማል ወይ ይቆማል ወይ
ምን ተባለ ብሎ ህይወት ይቆማል ወይ

ልፋትህ ላይ ያልነበረው
የአንተ ስኬት ያባነነው
ከመንገድህ እንዳይገታህ
አሉባልታው እንዳይረታህ

ድካምሽ ላይ ያልነበረው
የአንቺ ስኬት ያባነነው
ከመንገድሽ እንዳይገታሽ
አሉባልታው እንዳይረታሽ