Nhatty Man ተው በሉት ይኼን ሠው Tew Belut ናቲ ማን



Published
ተው በሉት ይኼን ሠው
አይተናኮልብኝ አይንካው
ወገኔን ሐገር አንደሌለው አያርገው
የማንነቴን መለኪያ ቤቱን ናፋቂ ስጋ ወ ደሜ
ጭንቁን መስማት እኔ ልሻም ሲቃው ሲከር ይመራል ሰላሜ
የጠንካራ ዕምነት ባለቤት
እግር ጥሎት ሲዘልቅ ካንተ ቤት
ፍቅርን ታጥቆ ነበር የመጣው
ከጥንት አባቱ ያንተን ካኖረው

ሊሰበስበን ፈልጎም ይሆናል
ነገር ለበጎ ለምክንያት ይመጣል
ግን ተው በሉት አይንካው ይኄ ሠው
ወገኔን አይግፋው ሐገር እንደሌለው

ተው በሉት ይኼን ሠው
አይተናኮልብኝ አይንካው
ወገኔን ሐገር አንደሌለው አያርገው

ቀን ከፍቶ ከቀየው ቢያርቀው
ማንም እንዳይንቀው
መች ሆነ የሷ ስደት ለአንድ ነፍሷ
ርቃ መገስገሷ
ቀን ከፍቶ ከሀገሯ ቢያርቃት
ማንም እንዳይንቃት
Nhatty Man (ቻቹ)

Music & lyrics by Nhatty Man
Music Arrangement, Mixing & Mastering by Robel Mehari.