Error inserting record: Duplicate entry '216.73.216.190-2026-07-08 19:32:14' for key 'ip_address_date_index' Nhatty Man & The Lalibelas አይከፋ ገፅሽ (አንድ ነገር) "Andneger" ናቲ ማን

Nhatty Man & The Lalibelas አይከፋ ገፅሽ (አንድ ነገር) "Andneger" ናቲ ማን



Published
ለዓይኔ ብርቁን ንቄው
አንቺን ብዬ ሁሉን ትቼው
ያለኝን ጭኜ አሟጥጬ
እስክመጣ አንዴ ቆርጬ
አንድ ነገር ይዤ እስክዘልቅ ደጅሽ
ፈገግ ብሎ ይቆየኝ አይከፋ ገጽሽ
መቻል ልቤን አስተምሬው
ደግ ቀን ይመጣል ብየ ዘክሬው
ባለሁበት ሁሉ ስፍራ
በክብርሽ ኮርቼ በስምሽ ስጠራ
ካንቺ ሐሴት በላይ ለኔ ደስታ
ምንስ ልቆ ሊገኝ ያንቺን ውለታ
የአቅሜን ያለኝን
እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ
ይዤ እቀርባለሁኝ
አንድ ነገር ይዤ እስክዘልቅ ደጅሽ
ፈገግ ብሎ ይቆየኝ አይከፋ ገጽሽ
ደም ግባት ቁንጅናሽ አንዳማረ ይቆየኝ
ሰላምሽን እንጂ ክፉ አያሰማኝ
ባለሁበት ሁሉ ስሜ መጠሪያዬ
መታወቂያ ጌጤ ኑሪልኝ ተስፋዬ
ናፍቆት አንገብግቦት ሲዳክር የዋለ
ጉያሽን አልሞ ሲዋልል ያደረ
አለ ኸዚ መንደር ራቅ ካለ ስፍራ
ስምሽ ሲጠራ ልቡ የሚመታ
ኑሮውን አልሞ ከቤትሽ የሸሸ
ከማያቀው መንደር ዉሎ አድሮ ያመሽ
ቸር ወሬን ጠባቂ ናፋቂ ያንቺን ጓዳ
በጥሩሽ የሚስቅ በክፉሽ ሚጎዳ
አንድ ነገር ይዤ እስክዘልቅ ደጅሽ
ፈገግ ብሎ ይቆየኝ አይከፋ ገጽሽ