Error inserting record: Duplicate entry '216.73.216.60-2025-10-25 00:34:46' for key 'ip_address_date_index' Nhatty Man - አይበቃ - Karaoke ናቲ ማን - Aybeka - ማጀብያ ሙዚቃ እና ግጥም - New Ethiopian Music 2020

Nhatty Man - አይበቃ - Karaoke ናቲ ማን - Aybeka - ማጀብያ ሙዚቃ እና ግጥም - New Ethiopian Music 2020



Published
#አይበቃ #nhattyman
Subscribe for more ...
https://www.instagram.com/nhatty_man/?hl=en
https://www.facebook.com/realNhattyman/
https://www.nhattyman.com

ሁሌ እንግዳ ፍቅር አይጠገብ
ተወኝ አይሉት ማብቂያም የለው ገደብ
እኔን ካንቺ ቀላቀለኝና
ደስታ ጣሙን ቸረኝ እንደገና
ያፈቀረ የማይወደው ስሜቱን
ከልቡ ሰው ለአፍታ መለየቱን
አብረን ስንሆን ጊዜ ይከንፍብኛል
ስትሄጂ ማጣሽ ማጣሽ ይመስለኛል

ተነፋፍቆ ለተገናኘ ሰው
ለጨዋታ ቀን ሌቱም አይበቃው
ናፍቆት ስንቁ ለነበር ትዝታው
ተነፋፍቆ ለተገናኘ ሰው

አይበቃ
ቀን ሌቱም አይበቃ
ጊዜውም ይነጉዳል
ፍቅሬ ስሆን ካንቺ ጋራ

አይበቃ
(አይበቃ)
ሰአቱም ይከንፋል
ፍቅሬ ስሆን ካንቺ ጋራ
(አይበቃ)

ለልብ ወግ ሲገኝ የልብ ሰው
ለምንድነው ሰአቱ የሚነጉደው
ለልብ ወግ ሲገኝ የልብ ሰው
ለምንድነው ሰአቱ የሚነጉደው

ተነፋፍቆ ለተገናኘ ሰው
ለጨዋታ ቀን ሌቱም አይበቃው
ናፍቆት ስንቁ ለነበር ትዝታው
ለጨዋታ ቀን ሌቱም አይበቃው