Nhatty Man - መዳፍሽ ይባረክ - Karaoke ናቲ ማን - Medafish Ybarek - ማጀብያ ሙዚቃ እና ግጥም - New Ethiopian Music



Published
ጥቂት ልበል ላውራ ልመስክር እኔም በተራዬ
ባይኖርም ቢቸግርም ቢጠፋ ቃል ለውለታሽ ላንቺ እምዬ
በቀጣኝ በገራኝ ያለስስት ከአፍሽ ነጥቆ ባጎረሰኝ
ልጀምር ከእሱ ይሁን ብለሽ ምርቃቴን ተቀበይኝ

መዳፍሽ ይባረክ አመድ አፋሽ አያርገው
ዘመንሽ ይለምልም እድሜሽን ያርዝመው

ከአዕምሮ በላይ ነው ውለታሽ አቻም የለው
ቅኔ ዜማ ቢደረደር ችሎ የማይገልጸው
የፍቅር ትርጉም ኖረሽ ያሳየሽን
ኑሪልን ክረሚ ክፉ አይንካሽ አንቺን

መዳፍሽ ይባረክ አመድ አፋሽ አያርገው
ዘመንሽ ይለምልም እድሜሽን ያርዝመው

ኑሪልኝ
አዎ ኑሪልኝ
ከነጉብዝናሽ ከነሙሉ ግርማሽ
ክፉ እንዳይነካሽ ኑሪልኝ ደምቀሽ

መዳፍሽ ይባረክ አመድ አፋሽ አያርገው
ዘመንሽ ይለምልም እድሜሽን ያርዝመው

ያኑርሽ ዘላለም…..