Teddy Afro - Selame (ሰላሜ) / Bado (ባዶ)



Published
ዋሽቶ ለመኖር አፌ አይችልም ከቶ
ታምኖ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ
ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም
ገንዘብ ለማግኝት ብዬ አላጣም ሰላም

እኔ አላጣም ሰላም….አላጣም ሰላም

ይህ ዓለም ንዋይ ጭኖ ወርቁን በሙዳይ
ማርኮት ከረታት ነፍሴን ከሰጣት ጉዳይ
ህሊና ሲያጣ ሰላም ወርቅ አልማዝ ሞልቶ
ሳይተኙ ማደር ሊሆን ከራስ ተጣልቶ

ከዚህ ሁሉ ቅጣት : ይሻላል ማጣት
አስኮንኛት ነብሴን : አልሞላም ኪሴን

ነብሴ እጅ እንዳትሰጪው ለኪሴ ….ታጣይኛለሽ ከራሴ
ሰላሜ እረፍት ያለብሽ መኝታ ……ታምነሽ አኑሪኝ ከጌታ

አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር
ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ
ያሉኝታ ከማጣ ዛሬ ገንዘብ ልጣ
አስገምቼው እራሴን አልሞላውም ኪሴን
ባዶ ላርገው ኪሴን፡ ባዶ ላርገው ኪሴን

ዋሽቶ ለመኖር አፌ አይችልም ከቶ
ታምኖ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ
ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም
ይሄን ለማግኘት ብዬ አላጣም ሰላም…እኔ አላጣም ሰላም
አላጣም ሰላም፡ እኔ …አላጣም ሰላም

የአመል ነው እንጂ ደሃ፡ የገንዘብ የለም
ሰው ባይኖር እይዋት እራሷን፡ ባዶ ናት አለም
ገንዘብ ብቻ ነው ያለ፡ የዚህ አለም ደስታ
ዳግም ይሸጣል ስሞ፡ ቢመለስ ጌታ

ለሰላሣ ዲናር …ሊያጣ ነብስ ይማር
አስኮንኛት ነብሴን ….አልሞላም ኪሴን

ግጥም ፤ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
ዜማ ፥ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

Enjoy! Subscribe!

Connect with us for more.
https://www.facebook.com/TeddyAfroMusic/
https://www.instagram.com/teddyafromuzika/
https://store.cdbaby.com/Artist/TeddyAfro1
https://itunes.apple.com/us/artist/teddy-afro/id457707367
https://www.vevo.com/artist/teddy-afro
http://www.dailymotion.com/teddyafro
https://twitter.com/teddyafromusic
www.teddyafromuzika.com

© All rights reserved to Teddy Afro