Nhatty Man ናቲ ማን - መዳኛው (ክግጥም ጋር) Medagnaw - New Ethiopian Music 2018



Published
መዳኛው
አይነ ግቡ ልብሷን የጥለቷን ቀልም
አብረው ያጎሉት አድምቀው ለዓለም
(እኛ የእነሱ ልጆች)
ልዩነትን ሽረው ፈቅደው ያለፉላት
የከበረ ስሟን ወድቀው ያቆሙላት
(እኛ የእነሱ ልጆች)
እኛ ይኄ ይንገስ ያ ይንገስ እየለያየን
አራራቀን እንጂ ፈውስ አልሆነን
ከአንተ የእኔ ዘር ይሻል ይሉት ቃል
አደከመን እንጂ መች ጠቅሞን ያውቃል
መዳኛው አንድ ፍቅር ነው
መዳኛው አንድ ፍቅር ነው
የኩራት ጥጋችን መማር መቁጠራችን
መላ ካልዘየደ ለአብሮነታችን
(እኛ የእነሱ ልጆች)
ዘመን አዘመነን ሰለጠንን ያልነው
ዓለም አንድ ስትሆን እኛ የተበተነው
(እኛ የእነሱ ልጆች
ይኄ ይንገስ ያ ይንገስ እየለያየን
አራራቀን እንጂ ፈውስ አልሆነን
ከአንተ የእኔ ዘር ይሻል ይሉት ቃል
አደከመን እንጂ መች ጠቅሞን ያውቃል
መዳኛው አንድ ፍቅር ነው
መዳኛው አንድ ፍቅር ነው
የኛ ነው የኛ
የኛ የኛ
ያንተም የኔ ነው የኔም ያንተው
ለሌላም ይተርፋል በፍቅር ከያዝነው
ይኅቺ ታላቅ ምድር በኩራት የቆመች
ማዘኗ ይበቃል በኛ ትካሳለች
በኖረው ወጋችን በእናት በአባት ልማድ
ቤትህ ቤቴ ነው በል ሳንመርጥ እንዋደድ
ከወቀስነው በላይ እንዳንሆን ተወቃሽ
በል ና እንነሳ እንሁን ታሪክ አዳሽ
የኛ ነው የኛ
የኛ የኛ
እስኪ መላ አምጣ ለተራበ አንጀት
ወገን ስቆ ይደር በዕውቀጥ ኩራበት
ከወቀስነው በላይ እንዳንሆን ተወቃሽ
በል ና እንነሳ እንሁን ታሪክ አዳሽ
https://www.facebook.com/realNhattyman
https://www.instagram.com/nhatty_man