Ethiopian music with lyrics - Abdu Kiar - Merkato Sefere አብዱ ኪያር - መርካቶ ሰፈሬ - ከግጥም ጋር



Published
Subscribe to @Abdu Kiar on YouTube: https://www.youtube.com/c/AbduKiarMusic


Follow Abdu Kiar online
Facebook : https://www.facebook.com/abdukiarmusic
Instagram : https://www.instagram.com/abdukiarofficial
Twitter : https://twitter.com/abdu_kiar
Spotify : https://artists.spotify.com/c/artist/2B8c0XLWWKbFmgSKDruKk4/profile/overview
Apple Music : https://music.apple.com/us/artist/abdu-kiar/493281808

መርካቶ ሰፈሬ - አብዱ ኪያር
ላላላለሌ ላለሌ ለለላ
ላላላለሊለላ ላላላላላ

አንቺ አዲስ አበባ ማየቱን ተውሽ ወይ
አሳድገሽ ሲጠፉ የታሉ አትይም ወይ
ጨዋ ደግ ልጆችሽ ውበትሽ ናፍቋቸው
ተሰቃዩ ብዙ እባክሽ ጥሪያቸው
እንኳን ላሳደግሽው ጥሬሽን ለበላ
ለስንቱ ጎረቤት ሆነሻል ከለላ
እናታችን ሀገር ፍቅርሽ ለብቻው ነው
ደጅሽንስ ከፍተሽ ኑ ብትይን ምንድነው

መቼም የገባሁ ቀን ካገር ከመንደሬ
ደስታ ነው ሚሰማኝ ገና ሳየው መርካቶ ሰፈሬ
ችላ ችላ አትበይ አይተሽ መቸገሬን
ሌላ እናት የለኝም ካንቺ ሌላ ውቢቷ ሀገሬ

የወግ የልማዱን ሊያደርጉ ሲጥሩ
በያሉበት አገር ሃበሾች ሲባሉ
ሲሰበሰቡማ ሲደምቅ ጨዋታቸው
አንቺ ነሽ አዎ ሸገር ትልቋ አርዕስታቸው
ጤፍ እንኳን ባይገኝ በማሽላ እንጀራ
ያገር ቀሚስ ለብሳ እህታችን ስትኮራ
በነጭ በዐረብ ሃገር ቢሆንም ኑሯቸው
ኢትዮጵያን ማየት ነው ትልቁ ህልማቸው

መቼም የገባሁ ቀን ካገር ከመንደሬ
ደስታ ነው ሚሰማኝ ገና ሳየው መርካቶ ሰፈሬ
ችላ ችላ አትበይ አይተሽ መቸገሬን
ሌላ እናት የለኝም ካንቺ ሌላ ውቢቷ ሀገሬ
Nobody can fix it up
Nobody can bring peace up
Africans are always out
While dem love dem green land
Who is gonna be blamed for this
When at last war, not a peace
Ethiopians in somebody’s land
Calling as a refugees
Di love I have got for Addis Ababa
And the people who is living there
I can’t wait until I see my hood
Until I breeze natural air
Only lord can make me live
Peacefully in a zion land
My wish in a paradise
In Addis Ababa town
መቼም የገባሁ ቀን ካገር ከመንደሬ
ደስታ ነው ሚሰማኝ ገና ሳየው መርካቶ ሰፈሬ
ችላ ችላ አትበይ አይተሽ መቸገሬን
ሌላ እናት የለኝም ካንቺ ሌላ ውቢቷ ሀገሬ

ኧረ እኔስ ሃገሬን መርካቶ ሰፈሬን
ኧረ እኔስ ሃገሬን መርካቶ ሰፈሬን