Error inserting record: Duplicate entry '216.73.216.17-2026-04-30 05:56:31' for key 'ip_address_date_index' Ethiopian music with lyrics - Abdu Kiar - Altelashim አብዱ ኪያር - አልጠላሽም - ከግጥም ጋር

Ethiopian music with lyrics - Abdu Kiar - Altelashim አብዱ ኪያር - አልጠላሽም - ከግጥም ጋር



Published
Subscribe to @Abdu Kiar on YouTube: https://www.youtube.com/c/AbduKiarMusic


Follow Abdu Kiar online
Facebook : https://www.facebook.com/abdukiarmusic
Instagram : https://www.instagram.com/abdukiarofficial
Twitter : https://twitter.com/abdu_kiar
Spotify : https://artists.spotify.com/c/artist/2B8c0XLWWKbFmgSKDruKk4/profile/overview
Apple Music : https://music.apple.com/us/artist/abdu-kiar/493281808

እንዴት እንዴት እንደናፈቅኩሽ ልቤ ብዙ እንደተቸገረ
አላየሽም እንጂ ስቃዬን ብታይኝ ታዝኚልኝ ነበረ
ከጧት እስከማታ መዋከብ መልክ አጥቷል ውሎዬና አዳሬ
ጠልቼሽ አይደለም የምጠፋው እወቂልኝ ተረጂኝ ፍቅሬ

አልጠላሽም አልጠላሽም አልጠላሽም እኔ እወድሻለሁ
እንኳን መጥላት ያንቺን ክፉ ስሰማ እቆጣለሁ
የኔ ነህ ወይ? የኔ ነህ ወይ? አትበይኝ ግድ የለም
ካንቺ በቀር እንዳትሰጊ የማፈቅረው የለም

ያክርመን እንጂ ያቆየን እንጂ
ገና ብዙ አለ ለኔና ላንቺ
ፍቅር ጨምሮ ፍቅር ጨምሮ
ያሳካው ጌታ ይሄንን ኑሮ
አይዞሽ ፍቅርዬ ምንም አትፍሪ
እኔ ያንቺው ነኝ አትጠራጠሪ
ፈራሁ አትበይኝ ምን ያስፈራሻል
ከራሱ በላይ ልቤ ይወድሻል
አሃሃሃሃ ሆሆ ዋዋዋዋዋ

እንዴት እንዴት እንደናፈቅኩሽ ልቤ ብዙ እንደተቸገረ
አላየሽም እንጂ ስቃዬን ብታይኝ ታዝኚልኝ ነበረ
ኑሮ ነው ብክን የሚያደርገኝ መልክ አጥቷል ውሎዬና አዳሬ
ጠልቼሽ አይደለም የምጠፋው እወቂልኝ ተረጂኝ ፍቅሬ

አልጠላሽም እኔ እወድሻለሁ
እንኳን መጥላት ያንቺን ክፉ ስሰማ እቆጣለሁ
የኔ ነህ ወይ? የኔ ነህ ወይ? አትበይኝ ግድ የለም
ካንቺ በቀር እንዳትሰጊ የማፈቅረው የለም

በይ የኔ ፍቅር እንዳልኩሽ አርጊ
ጠልቶኛል ብለሽ ከቶ እንዳትሰጊ
በይ የኔ ፍቅር የፍቅር መናኝ
ሰላም ቆይልኝ እስክንገናኝ
ሃሳቡን ትተሽ መጠራጠሩን
በርቺልኝ ብቻ አጥብቀሽ ፍቅሩን
የምመጣ ቀን የመጣሽ ለታ
የፍቅር ውሎ የፍቅር መኝታ
አሃሃሃሃ
ሆሆ
ዋዋዋዋዋ….