Ethiopian music with lyrics - Abdu Kiar - Jiwa Jiwe አብዱ ኪያር - ዥዋ ዥዌ - ከግጥም ጋር



Published
Subscribe to @Abdu Kiar on YouTube: https://www.youtube.com/c/AbduKiarMusic


Follow Abdu Kiar online
Facebook : https://www.facebook.com/abdukiarmusic
Instagram : https://www.instagram.com/abdukiarofficial
Twitter : https://twitter.com/abdu_kiar
Spotify : https://artists.spotify.com/c/artist/2B8c0XLWWKbFmgSKDruKk4/profile/overview
Apple Music : https://music.apple.com/us/artist/abdu-kiar/493281808

ዥዋ ዥዌ - ግጥምና ዜማ አብዱ ኪያር 2008 ዓም

እንደ ዥዋ ዥዌ ሆኗል ነገሯ
እምነትም ጽናትም የለውም ፍቅሯ
እንደ ዥዋ ዥዌ ሆኗል ነገሯ
ወደ ሞቀበት ነው ውሎና አዳሯ

ጠፍታ ጠፍታ ርቃ ሰንብታ
ስፈልጋት ቀንና ማታ
ድንገት ትመጣና ከቤቴ
ፍቅሬ ነህ ትላለች ህይወቴ
የኔ ነች የኔ ነች እልና
ትጠፋለች ደግሞ እንደገና
እውነትን መናገር ፈርታለች
እዚም እዛም ፍቅር ትላለች

እንደ ዥዋ ዥዌ ሆኗል ነገሯ
እምነትም ጽናትም የለውም ፍቅሯ
እንደ ዥዋ ዥዌ ሆኗል ነገሯ
ወደ ሞቀበት ነው ውሎና አዳሯ

እዚጋ ስትሆን እዛ ይታያታል
እዛጋ ስትሆን እዚህ ያምራታል
አልወደደችኝ ወይ አልጠላችኝ
እያመነታች አሰቃየችኝ
ወዳኛለች ስል ትርቀኛለች
ቀረበችኝ ስል ትሸሸኛለች
አልወደደችኝ ወይ አልጠላችኝ
እያመነታች አሰቃየችኝ
ዥዋ ዥዌ….. ዥዋ ዥዌ…… ዥዋ ዥዌ…….

ፍቅር ፍቅር ፍቅር እያለች
በየቦታው በሰው ታምናለች
ቃላቱ ላይ ብትችልበትም
ተግባሩ ላይ የለችበትም
እውነትን መናገር የፈራ
ስለ ፍቅር ቢሰብክ ቢያወራ
አይዘልቅም አይዘልቅም አይዘልቅም
ፍቅር ዥዋዥዌን አያውቅም

እንደ ዥዋ ዥዌ ሆኗል ነገሯ
እምነትም ጽናትም የለውም ፍቅሯ
እንደ ዥዋ ዥዌ ሆኗል ነገሯ
ወደ ሞቀበት ነው ውሎና አዳሯ

እዚጋ ስትሆን እዛ ይታያታል
እዛጋ ስትሆን እዚህ ያምራታል
አልወደደችኝ ወይ አልጠላችኝ
እያመነታች አሰቃየችኝ
ወዳኛለች ስል ትርቀኛለች
ቀረበችኝ ስል ትሸሸኛለች
አልወደደችኝ ወይ አልጠላችኝ
እያመነታች አሰቃየችኝ
Playa Playa Playa Playa, how long you wanna stay playa?