Ethiopian music with lyrics - Abdu Kiar - Zoro Zoro Adam አብዱ ኪያር - ዞሮ ዞሮ አዳም - ከግጥም ጋር



Published
Subscribe to @Abdu Kiar on YouTube: https://www.youtube.com/c/AbduKiarMusic


Follow Abdu Kiar online
Facebook : https://www.facebook.com/abdukiarmusic
Instagram : https://www.instagram.com/abdukiarofficial
Twitter : https://twitter.com/abdu_kiar
Spotify : https://artists.spotify.com/c/artist/2B8c0XLWWKbFmgSKDruKk4/profile/overview
Apple Music : https://music.apple.com/us/artist/abdu-kiar/493281808

ምንድነህ አለችኝ ኧረ ምን ልበላት
ጥቁር ሀበሻነት ከፊቴ እየታያት
አታውቀኝ እንዳልል ስንት አሳልፈናል
ጠብቂያት ጠብቃኝ ፍቅርን ተካፍለናል

ምንነጋገርበት ቋንቋው አንድ አይነት
አዲስ ከተማ ነው የተማርንበት
ምንድነህ ትላለች መልሱልኝ ሀገር
እኔስ የሚገባኝ ሰው መሆኔ ነበር

ሁሉም ውስጡ ስጋ ና ደም
ቀለም መልኩ ቢለያይም
ወላጁ አንድ ነው
አባቱ አንድ ነው
ዞሮ ዞሮ አዳም

ብዙ ተባዙ ሲል ሂዱ አለምን ሙሏት
እንድትመቸን አርጎ መሬትን ሲሰራት
እንዳንለያይ ነበር መፅሀፉን ማውረዱ
መች ሀረግ ልንቆጥር ሆኖ አንድ ያዳም ግንዱ

እኔነቴን ወዳ እንድታውቅ ማንነቴን
ቆጠራ ልግባ ወይ አያት ቅድም አያቴን
ምንድነህ ብላለች ሰው ነኝ ልላት ነው
ነጭ ጥቁር በአለም ሁሉም ያዳም ልጅ ነው

ሁሉም ውስጡ ስጋ ና ደም
ቀለም መልኩ ቢለያይም
ወላጁ አንድ ነው
አባቱ አንድ ነው
ዞሮ ዞሮ አዳም