Ethiopian music with lyrics Abdu Kiar and Melat Kelemework ወዬ ወዬ አብዱ ኪያርና ሜላት ቀለመወርቅ



Published
Subscribe to @Abdu Kiar on YouTube: https://www.youtube.com/c/AbduKiarMusic


Follow Abdu Kiar online
Facebook : https://www.facebook.com/abdukiarmusic
Instagram : https://www.instagram.com/abdukiarofficial
Twitter : https://twitter.com/abdu_kiar
Spotify : https://artists.spotify.com/c/artist/2B8c0XLWWKbFmgSKDruKk4/profile/overview
Apple Music : https://music.apple.com/us/artist/abdu-kiar/493281808

ወዬ ወዬ
ግጥምና ዜማ አብዱ ኪያር


ፍቅርዬ ወዬ ወዬ
የኔ አለም ወዬ ወዬ
እኔ ናፍቄሃለው አንገናኝም ወይ

ፍቅርዬ ወዬ ወዬ
የኔ አለም ወዬ ወዬ
እኔ ናፍቄሻለሁ አንገናኝም ወይ

እኔን ጭምቷን ልጅ ለምነህ አባብለህ
እንደዚህማ አትጠፋም በፍቅርህ ሰው ገለህ
ያኔ በቀን በቀን እንዲያ እንዳልፈለግከኝ
ዛሬ ስትጠፋ ፈራሁኝ ጨነቀኝ
ፍቅርዬ ወዬ ወዬ
የኔ አለም ወዬ ወዬ
እኔ ናፍቄሃለው አንገናኝም ወይ

መች ጠፋሁ መች ጠፋሁ አልሞላ ብሎ እንጂ
ድሮም ልብ የለኝም የሚጨክን ባንቺ
ረጋ ሲሉ ይጥማል ፍቅር ሩጫ አይችልም
ድሮም እልሽ ነበር አሪፍ አይቸኩልም አዎ
ፍቅርዬ ወዬ ወዬ
የኔ አለም ወዬ ወዬ
እኔ ናፍቄሻለሁ አንገናኝም ወይ

ቦታ ምረጥልኝ ቦታ ማታ እንድንገናኝ ማታ
ፍቅሬ ላይህ ቸኩያለሁ ቦታ ምረጥ አንድ ቦታ
ማታ የምናቃት ቦታ ማታ የምናቃት ቦታ
ፍቅሬ የቀደመ ይጠብቅ ማታ እኔ አልቀርም ማታ
ፍቅርዬ ወዬ ወዬ
የኔ አለም ወዬ ወዬ
እኔ ናፍቄሃለው አንገናኝም ወይ
ፍቅርዬ ወዬ ወዬ
የኔ አለም ወዬ ወዬ
እኔ ናፍቄሻለሁ አንገናኝም ወይ

ልቤ አምጪው ይለኛል እንቅልፍ አጥቷል አይኔ
ፍቅር እንዲህ መሆኑን መች አወቅኩኝ እኔ
ያኔ ፍቅርን ሳላውቅ ምንም ሳልረዳህ
ዛሬ ነው የገባኝ ብዙ እንደተጎዳህ
ፍቅርዬ ወዬ ወዬ
የኔ አለም ወዬ ወዬ
እኔ ናፍቄሃለው አንገናኝም ወይ

ልጅነት ነው እንጂ ክፋት የለብሽም
ገና አፈቅርሻለሁ አልቀየምሽም
እንኳን ፍቅሬ ገባሽ እንኳን ተረዳሽኝ
እቅፍ አርጊኝና ከህመሜ ፈውሺኝ
ፍቅርዬ ወዬ ወዬ
የኔ አለም ወዬ ወዬ
እኔ ናፍቄሻለሁ አንገናኝም ወይ

ቦታ ምረጥልኝ ቦታ ማታ እንድንገናኝ ማታ
ፍቅሬ ላይህ ቸኩያለሁ ቦታ ምረጥ አንድ ቦታ
ማታ የምናቃት ቦታ ማታ የምናቃት ቦታ
ፍቅሬ የቀደመ ይጠብቅ ማታ እኔ አልቀርም ማታ
ፍቅርዬ ወዬ ወዬ
የኔ አለም ወዬ ወዬ
እኔ ናፍቄሃለው አንገናኝም ወይ
ፍቅርዬ ወዬ ወዬ
የኔ አለም ወዬ ወዬ
እኔ ናፍቄሻለሁ አንገናኝም ወይ
ፍቅርዬ ወዬ ወዬ
የኔ አለም ወዬ ወዬ
እኔ ናፍቄሃለው አንገናኝም ወይ
ስጠራሽ ወዬ ስትጠሪኝ ወዬ ወዬወዬ ወዬወዬ
ስጠራህ ወዬ ስትጠራኝ ወዬ ወዬወዬ ወዬወዬ