Nhatty Man ናቲ ማን - ምን ነበረ ያልከኝ? ግጥም Min Nebere Yalkegn? Amharic poetry



Published
ምን ነበረ ያልከኝ?

ከቀዬህ ስትርቅ
ለምን አንደወጣህ
ሐሳብህ ግልጽ ነው፤
ካንተነትህ በልጦ ያጎረሰህ እጅዋ፣
አንዳይወቅስኽ ፈርተህ፣
ጡሬያት ልለፍ ብለህ፣
ጛጉተህ አንደተሰደድኽ፣
ሳትነግረኝ አውቃለው፤
ልቡናኽ ቢያምነውም ፈተና እንዳለው
ከእኔ አንዲቷ ነፍስ
የእምዬ ጛዳ ክብሩ ይበልጣል ብለህ፣
ስትርቅ ስትሰደድ፣
በጥቂቱም ቢሆን ሳትነግረኝ አውቃለው፤
ወንድነትኽን ከቶ በማያውቀው መንደር፣
ፍቅር ባልጎበኘው የክፉ ወታደር፣
ሕልምህን ሊያጨልም ሲነዳህ ወደ ሞት፣
ምን ነበረ ያልከኝ? ባወኩት ወንድሜ፣
በስትንፋስኽ ዘመን በዛች ቅፅፈተ ዕድሜ፤
ምን ነበር ሐሳብህ?
ታግቶ የቀረው ካፋፍ ከከንፈርህ፣
ልትል የፈለከው ያተምከው ከገጽህ፤
የተጠማው ምድር እስኪርስ በረሐው
ምን ነበረ ያልኸኝ አንተ ስትዘጋጅ፣
ንፁሕ ደም ሊቀዳ፣ሲደገስ፣ሲቦካ
ስትቀርብ ለአሸዋው።

“ማስታወሻነቱ ህይወታቸው በከንቱ ላለፈው ወገኖቻችን ይሁንልን

ፈጣሪ ለቤተሰቦቻቸዉ መፅናናትን ያድልልን “

ግጥም ናትናኤል አያሌው (Nhatty Man)

አጃቢ ሙዚቃ ዮሴፍ ሃይለማርያም
ሚያዝያ ፪ሺህ፯/2015