Nhatty Man - Yeseqelut (sendeqea) ናቲ ማን - የሰቀሉት(ሰንደቄ ) - New Album 2023 - አዲስ አልበም 2015 e.c



Published
አልበሙን በመግዛት ድጋፎን ማሳየት ከፈለጉ
https://realnhattyman.bandcamp.com/album/vol-4

Supported by the Australian Government through the Australia Council for the Arts, its arts funding and advisory body.

፯ የሰቀሉት

ስንቶች የወደቁለትን
እኛ እየተውነው
ሌላ ሲደምቅበት ባይ
እላለሁ እላለሁ
ኩሪበት ኩራበት
ኩሩበት እንኩራበት
ከፍ አድርጉት
እናንሳው

አረንጏዴ ብጫ ቀይ ሰንደቄ

ቢወዱን ቀድመው ወደቁልን ቢወዱን
ሊያከብሩን ለመኖር ሳይሳሱ ሊያነግሱን
ለፍቅራቸው በኛ ትንሽ እውቀት ለማንዳኘው
አርማው ነው ያነሱት ለሠው ክብር ወድቀው

ሲታይ ከሩቅ ነዛሪ
ታሪክን ሞጋች መስካሪ
ከፍ አድርገው የሰቀሉት
ሰውን እኩል የወደዱት
የ ፫ ቀለማት ህብር የ አትንኩኝ ባይነት አርማው
በድሉ ደምቆ የሚያበራው

ቅዱስ ምድር እያለ ተስፋም ለምያደርጋት
በሩቅ እያለመ ምድሯን እስኪረግጣት
በቀለሙ ለሚበደለው ለሚገፋው ተስፋው
ኩራት የክብር አርማው

ይሁን ብለው
የሰቀሉት ሰንደቁ ላይ
የሰቀሉት ዓድዋ ላይ

አረንጏዴ ብጫ ቀይ አርማዬ
የነፃነት ኩራት ልክ ግርማዬ

ሳር ቅጠሉን ቃኝተው
ከ ዓደይ ተስፋን ቀስመው
በ ደም ያደመቁት
ከፍ አድርገው የሰቀሉት

በ አንድነት ተመው
ለዕምነት ለሀገር ለሰው
ሁሉ ክብር ብለው
ንጉስ አምነው ተከትለው
ልዩነትን ወድያ ጥለው
በሰጡን ነፃነት እኛው ከተለያየንበት
አይሆንም

የሰው ልጅ በሰውነቱ ብቻ እንዲመዘን
በቆዳውም በአይኑ ቀለም ደግሞም
በቋንቋው አንዳይለያይ
እንዳይኖር የበታች የበላይ
ሙግት ገጥመው አልፎም ተዋድቀው
ኩሩበት እንካቹ ብለው ወድቀው
በሰጡን ነፃነት መልሰን እነሱኑ ከወቅስንበት ስኅተት
ይልቅ ያዘው ከፍ አድርገው የሩቁ እንደደመቀበት
አንተም ኩራበት