Yehunie Belay | New Single | BE ZEMEN MEBACHA "በዘመን መባቻ" 2017



Published
Yehunie Belay | New Single | BE ZEMEN MEBACHA "በዘመን መባቻ" 2017

Don't forget! Subscribe to my channel | አመሰግናለሁ!
Google+ : https://plus.google.com/u/0/110879127828427744133
Facebook: https://www.facebook.com/yehuniebelay/
Subscribe:-https://www.youtube.com/channel/UCwes_SbZuxuXMeYdnZcvAFQ


“በዘመን መባቻ”

ግጥምና ዜማ | ይሁኔ በላይ
ሙዚቃ ቅንብር | ሄኖክ ነጋሽ
Cover Photo by | Photo Clear|ደረጀ
2017

“በዘመን መባቻ”

እህ ዘመድ የናፈቀው ስንቁ እህህ ነው
እህ አገሩ የናፈቀው ስንቁ እህህ ነው
እህ በሰው ሀገር ያለ እህህ እንዳለ
እህ ለወገኑ ያደረ የተከበረ
እህ ህዝቡን ያከበረ የተከበረ
እህ እናት አባት ያለ ይታይ የታለ
እህ ወንድም እህት ያለ ይታይ የታለ
እህ ሆዱን የወደደ ቀረ እንዳበደ

እረዘመ! ረዘመ ረዘመ መንገዱ ረዘመ
ፍቅር እየራቀን የእውነት መንገዷ እየተጣመመ!
አማን ሁኝ! ሰላም ሁኝ ብቻ ደህና ሁኝ ብቻ
እድሜ ይስጠኝ ብቻ መጥቼ አይሻለሁ በዘመን መባቻ!

ይመሻል ይመሻል ይነጋል ይነጋል ቀን ይፈራረቃል
ያገሬ የወንዜ ትዝታ ለቤ ውስጥ ለቤ ውስጥ ይፈለቃል

ፍቅር የያዘው የወዘወዘው አይፈራም ጋሜ አይፈራም ያዥው
ፍቅር የያዛት የወዘወዛት አትፈራም ጋሜ አትፈራም ያዛት

ለራሱ ብቻ የሚኖር ዜጋ ላክልኝ ሲሉት አይሰማኝም ብሎ ሚዘጋ
አገር ወገኑን የሚዘነጋ አትወድም እናት አትወድም ቆንጆ
አታስከትልም አርጋ መናጆ
የተባረከ የተከበረ በየሄደበት ያስመሰከረ
አይለወጥም ወጉ ባህሉ ከአገሩ ርቆ ቢኖርም ቅሉ
የኢትዮጵያ ልጅ የሀበሻ ልጅ ለኔ ምትለው እሽ ምትለው
ራሱን ያልረሳ ለሀገር ወገኑ ወድቆ ሚነሳ የሀገሯን ልጅነው

ያዛት ያዛት ግጠማት ያገርህ ልጅ ወርቅ ናት
ያዥው ንኪው ግጠሚው ያገርሽ ልጅ ወርቅ ነው
ያዛት ያዛት ግጠማት ያገርህ ልጅ ወርቅ ናት
ያዥው ንኪው ግጠሚው ያገርሽ ልጅ እሱ ነው
እኔ ብቻ አንደኛ እኔ ነኝ ትክክል እኔ ከሞትኩኝ ሰርዶም አይብቀል
እኔ ብቻ አዋቂ እኔ ነኝ ምሁር የኔ ዘር ትልቅ ብሎ የሚምል
አትወድም እናት አትወድም ቆንጆ አትወድም እናት አትወድም ቆንጆ

ዘር አትቁጠሩ ዘር ለገበሬ አርሶ ሚያበላው እያለ ሀገሬ
እስቲ ሁላችን ፍቅር እንዝራ ለመጭው ትውልድ ለባለ አደራ
የሃበሻ ልጅ አትወድም ጉራ የኢትዮጵያ ልጅ አትወድም ጉራ
የኢትዮጵያ ልጅ የሀበሻ ልጅ ለኔ ምትለው እሽ ምትለው
ራሱን ያልረሳ ለሀገር ወገኑ ወድቆ ሚነሳ የሀገሯን ልጅነው

ያዛት ያዛት ግጠማት ያገርህ ልጅ ወርቅ ናት
ያዥው ንኪው ግጠሚው ያገርሽ ልጅ ወርቅ ነው
ያዛት ያዛት ግጠማት ያገርህ ልጅ ወርቅ ናት
ያዥው ንኪው ግጠሚው ያገርሽ ልጅ እሱ ነው
_ በይሁኔ በላይ 1/23/2017