Yehunie Belay "AWOY NURO" አወይ ኑሮ..! NEW MUSIC 2019 (Official Video)



Published
Ethiopian Music: Yehunie Belay | "AWOY NURO"አወይ ኑሮ...! NEW MUSIC 2019 (Official Video)

ውድ ወገኖቼ አድናቂዋቼ እንደምን አላችሁልኝ::
አዲስ ዜማ ላኩላችሁ!
መልካም ድምጫ!
Share and subscribe ! እወዳችሗለሁ!

አወይ ኑሮ!

አወይ ኑሮ አወይ ነገር 
እንዲ እያሉ ማሰብ አይቀር x2

ህልም ፈች አዋቂ እያየሁ መብዛቱን
ማስታወስ ከበደኝ ካቻምና ያለምኩትን 

እጅግ ናረ ቢሉኝ የበርበሬ ዋጋ
ያስነጥሰኝ ጀመር ልጠይቅ ስጠጋ

ማን ይጏዝ ነበረ በጎዳናው ጥበት
አንደኛው ሲወጣ አንዱ ባይወርድበት

አውራ አመልካች መሃል ቀለበት ትንሽ ጣት
ብሶት ያስወጣሉ በክራሩ ጅማት

አወይ ኑሮ! 
አወይ ኑሮ አወይ ነገር 
እንዲ እያሉ ማሰብ አይቀር x2

ላረግ ብዬ ተውኩት ማልዶ እንደ ወፍ ማዜም
ታርሶ የጎደለን ቤት ባይሞሉት በመልቀም

ሰው እሆናለሁ ብዬ ሳበዛ ሃሳብ ጭንቀት
ከራስ ፀጉሬ ቀድሞ ፊቴን በላው ሽበት

አርሰውና አጭደው ጎተራ ካልሞሉ
ጥላስ ይክብዳል ወይ አለሁ አለሁ ቢሉ

ገብስ ቆሎ መብላት የኔ ሆድ ሲያምረው
ፈታጊው ቸገረኝ በዝቶ ሚያምሰው

እህ እንዴነሽ ህይወት እህህ እስከዚያው
እህ የኑሮን ነገር እህ ቀን እስኪፈታው
እህ እህህ እንዳልን እህ መች እንቀራለን 
ዘመን ቢበድል እህ ይክሳል ዘመን
እህ መሽቶብን አይቀር እህ ጨልሞብን
እህ መተዛዘቢያው እህ ይወጣል ቀን
እህ እህህ መኖር እህ ብትወደጂም 
እህ ሰው ሳታደክሚ እህ ሳይለፉ አትሞይም

ነነነ ....,,,

አወይ ኑሮ
አወይ ኑሮ አወይ ነገር 
እንዲ እያሉ ማሰብ አይቀር x2

ህመም ገብቷል አሉኝ ሰው የሚያሸብር
የሚብስ ይመስል ከርሃብ ከችግር
እንግዲህ ይራበኝ ፆሜን ጠበቅ ላርገው
የሚያሲዘኝ ሰው ቢሆን ሚያስፈታኝ አምላክ ነው

ነነነ...,

ትንሽ ቢያራርቀን ያንድ ሰሞን ነገር
እንዴት ያወሩታል ዝምድና እንደሚቀር

እስቲ ማውራት ይቅር ደርሶ አናክፋ ነገር 
ደፍርሶ ሚታየን አድሮ መጥራቱ አይቀር

አወይ ኑሮ!

አወይ ኑሮ አወይ ነገር 
እንዲ እያሉ ማሰብ አይቀር x2

ተቃቅፈው ቢገፉት ተግባብተው በፍቅር
ከወገን አይበልጥም የችግሩ ቁጥር

ቀን ሚወራው ሁሉ ተስፋ ቢያስቆርጠኝ 
በግዜ ተጋደምኩ ደግ እንዲያሳልመኝ

ምንኛ ብልህ ነው የሰጠው ትዕግስቱን
እሱ ያብጀው ብሎ የሚገፋ ቀኑን

ስጠኝ እንቡል እንጂ ጤናና ትዕግስቱን 
አባይ ችሎ የለምወይ ሺህ ዓመት ሲባክን

እህ
እህ እንዴነሽ ህይወት እህህ እስከዚያው
እህ የኑሮን ነገር እህ ቀን እስኪፈታው
እህ እህህ እንዳልን እህ መች እንቀራለን 
ዘመን ቢበድል እህ ይክሳል ዘመን
እህ መሽቶብን አይቀር እህ ጨልሞብን
እህ መተዛዘቢያው እህ ይወጣል ቀን
እህ እህህ መኖር እህ ብትወደጂም 
እህ ሰው ሳታደክሚ እህ ሳይለፉ አትሞይም

ግጥም :- ፀጋዬ ደቦጭ
ዜማ:- ተዘራ ተችሎ

ሙዚቃ ቅንብር:- ሄኖክ ነጋሽ
ማንዶሊን:- አየለ ማሞ
ክራር:- ፋንታሁን አባተ

2019