Yehunie Belay - "AEND ADEREGEN" | አንድ አድርገን New music official Video



Published
Yehunie Belay - "AEND ADEREGEN" |" አንድ አድርገን" New music official Video

Please subscribe my Channel
Google+ :https://plus.google.com/u/0/
Facebook: https://www.facebook.com/yehuniebelay/
Subscribe:-https://www.youtube.com/user/YehunieBelay

የእርቅ ዘመን የሰላም ይሁን - በሀገራችን
ሰላም ፍቅር ይዝነብ ከሰማይ - ኢትዮጵያ ላይ
ተበታትነን እንዳንቀር ወጥተን - አንድ አድርገን
ተበታትነን እንዳንቀር ወጥተን - አንድ እንሁን
___________
ከዚያም ወዲህ መጣ - ከዚም ወዲያ ሄደ
አዲስ ላይ ተሳፍሮ - አስመራ ወረደ
ከአስመራ ተነስቶ- ኢትዮጵያ ወረደ
ከአሜሪካ በርሮ - አዲስ ላይ ወረደ
ካውሮፓ ተሳፍሮ - አዲስ ላይ ወረደ
አምባጓሮ ሞተ - እጅግ ተዋረደ
እልል እልል በሉ - ላይመለስ ሄደ!
___________
ተበታትነን እንዳንቀር ወጥተን - አንድ አድርገን
ተበታትነን እንዳንቀር ወጥተን - አንድ እንሁን
___________
ከፍ አድርጉት ባንዲራውን (ባንዲራውን)2
አርማ ጌጤን ምልክቴን (ባንዲራውን)2
ከፍ አድርጉት ባንዲራውን (ባንዲራውን)2
ያባቶቼን ያደራውን (ባንዲራውን)2
___________

ይቅር እንባባል - ፍቅር ያሸንፋል
በምድር የፈጠሙት - በሰማዩ ይደረሳል
እንደ አንድ ልብ መስክር - እንደ አንድ ቃል ተናገር
ጨለማው ተገፏል - የጋረደን ነገር
ከወንድማማች ጠብ - ከክፉ ሰውረን
የኢትዮጵያችን አምላክ - አንድ አርገህ አኑረን
ወደ ፍቅር ጉዞ - እጅ ለእጅ ተያይዘን
ካህናት ይባርኩን - በአራቱም ማዕዘን
ከፍ አርገህ አብራና - የመቅረዙን መብራት
ኢትዮጵያዬ እናቴን - ወደ ፍቅርህ ምራት
___________
እምዬን! እናቴን! እምዬን! ሀገሬን !
እምዬን! እናቴን! እምዬን! ኢትዮጵያን!
እምዬን! እናቴን! ክፉ አይንካሽ ሀገሬን!
___________
የእርቅ ዘመን የሰላም ይሁን - በሀገራችን
ሰላም ፍቅር ይዝነብ ከሰማይ - ኢትዮጵያ ላይ
ተበታትነን እንዳንቀር ወጥተን - አንድ አድርገን
ተበታትነን እንዳንቀር ወጥተን - አንድ እንሁን
___________
አገርና ህዝቡን - ወገኑን አክባሪ
እሱን ተማሪ አርጎ - ጋሼ የሚል መሪ!
ፈሪ አንገራጋሪው - ቀርቶ የበደለን
ይሄ ሰው ዘንድሮ - ዝቅ ብሎ ገደለን
ጓደኞቹን ይዞ - በፍቅር ገደለን!
ተበታትነን እንዳንቀር ወጥተን - አንድ አድርገን
ተበታትነን እንዳንቀር ወጥተን - አንድ እንሁን
___________
ከፍ አድርጉት ባንዲራውን (ባንዲራውን)2
አርማ ጌጤን ምልክቴን (ባንዲራውን)2
ከፍ አድርጉት ባንዲራውን (ባንዲራውን)2
ያባቶቼን የአደራውን (ባንዲራውን)2
___________
እስከመቼ ድረስ - አዝኖ ይኖራል ሰው
ልጅሽ ደረሰና - እምባሽን አበሰው
አሁን የት ይገኛል - ለወገኑ አሳቢ
ከያሉበት ቦታ - እንደ እናት ሰብሳቢ
___________
እምዬን! እናቴን! እምዬን! ሀገሬን !
እምዬን! እናቴን! እምዬን! ኢትዮጵያን!
እምዬን! እናቴን! ክፉ አይንካሽ ሀገሬን!
- ይሁኔ በላይ -7/21/2018