Ethiopian Music | Yehunie Belay - ይሁኔ በላይ | Gelagay - ገላጋይ | New Music Video (Official Video) 2021



Published
Yehunie Belay - ይሁኔ በላይ | Gelagay - ገላጋይ | (Official Video) 2021
#ይሁኔበላይ #Yehuniebelay #Ethiopia
ገቢው :-ቪዲዮው ለእናንተ ከደረሰ ከዛሬ ቀን ጀምሮ እስከ
አንድ ወር ባሉት ቀናት ውስጥ በዩቱብ ከሚገኜው
ገቢ በጦርነቱ ምክኒያት ለተፈናቀሉና ችግር ለደረሰባቸው
ንፁሃን ወገኖቼን ይረዳ ዘንድ ምክንያት ይሁንልኝ::
ይሁኔ በላይ
2014 ዓ.ም

ይህ የይሁኔ በላይ የዩቲብ ቻናል ነው:: በየጊዜው ለሚለቀቁ ስራዎች በቀጥታ እንዲላክላችሁ ቻናሉን ሰብስክራይብ ማድረግ አይርሱ:: እናመሰግናለን::
Make sure to subscribe to Yehunie Belay YouTube Channel and turn on notifications to stay updated
https://www.facebook.com/yehuniebelay...
https://www.instagram.com/yehuniebelay

ይሁኔ በላይ
ገላጋይ!

እሷ የኔ ጉዳይ : እሱ ፍቅር አጉዳይ
ከበሬ ቆሜያለሁ ፡ አልሞት ባይ ተጋዳይ
ሰላም ሲሉት ዘራፍ ፡ ወዲያ ሲሉት ወዲህ
በእጄ እንዳይጠፋብኝ ፡ ገላግሉት እንግዲህ

ኦሆ ገላጋይ ገላጋይ (4)

ቆይማ ቆይማ : ላሳየው ቆይማ !
አንችን ብሎ መጥቷል : ነገር የተጠማ!
ደሞ ለወንድነት : ድሮም አልታማ!
ባንቺ ይፈትኑኝ : ይታይ የኔ ግርማ!

በፊት ይገለጣል : በአይን የማይነገር
እስቲ ገለል በሉ : ወዲ አለ ነገር
ከወጪ ወራጁ : ብጫወት ብስቅም
ባንቺ ከመጡብኝ : እኔ ዋዛ አላውቅም

ቢሻው በማባበል : ቢሻው በሽመሉ
ይመለስ የለም ወይ : ሁሉም እንደ አመሉ
እንደምናውቅበት : በፍቅር ማስከር
መቼ እናጣዋለን : ጥሎ መፎከር

ኦሆ ገላጋይ ገላጋይ (4)
ኦሆ በአንድ ዱር ይበቅላል : በትርና አባባ
በልምምጥ ባይሆን : ለምጠኸው ግባ
ገባ ገባ ይበል : ልብ ያለው ተማምኖ
ይመለሳል ገና : እንዳልነበር ሁኖ
ኦሆ ገላጋይ ገላጋይ !(4)

ቆይማ ቆይማ : ላሳየው ቆይማ !
አንችን ብሎ መጥቷል : ነገር የተጠማ!
ደሞ ለወንድነት : ድሮም አልታማ!
ባንቺ ይፈትኑኝ : ይታይ የኔ ግርማ!

አወይ አለማፈር : አወይ ስራ ማጣት
ያልዘሩትን ማሳ : ልጨድ ብሎ መምጣት
አለሁልህ በይኝ : አለሁልሽ ውዴ
መመከትም ያውቃል : ያንተራሰሽ ክንዴ

ቤት ለእንግዳ ብዬ : ሞሰቤን ባጋራ
ልካፈልህ አለኝ : አንቺን ባላጋራ
ሲያዩሽ ዝም አልኋቸው : አይን አይታገድም
ኩራቴ ነሽና : ሲነኩሽ አልወድም

ኦሆ ገላጋይ ገላጋይ (4)
አንቺን ብሎ ወጥቶ : ጀግና እንዴት ይረታል
እንኳን ብትር ቀርቶ : ሞገድ ይመከታል
እንደ ስመጥሩ : እንደ አበጀ በለው
ትዕግስት ብቻ አይደለም : ክንዴ ብርታት አለው

ኦሆ ገላጋይ ገላጋይ (4)
ፍርሃት ማነው ቢሉኝ : ስሙን አላውቀውም
ሞትን በቁሜ እንጅ : ሞቼ አልጠብቀውም
ወዲህ ወዲያ የለም : ቀና ነው ነገሬ
ዋዛ መቼ አዉቃለሁ :ባንቺና በአገሬ
ገላጋይ!

ግጥም ፡ በእዉቀቱ ስዩም
ዜማ ፡ ተዘራ ተችሎ