Featured

Ethiopian Music : Yehunie Belay ይሁኔ በላይ ( አይሞሎ) New Ethiopian Music 2020 #Awi #Aymolo #Agew



Published
Yehunie Belay ይሁኔ በላይ ( አይሞሎ) New Ethiopian Music 2020 (Official Video)
ይህ የይሁኔ በላይ የዩቲብ ቻናል ነው:: በየጊዜው ለሚለቀቁ ስራዎች በቀጥታ እንዲላክላችሁ ቻናሉን ሰብስክራይብ እና ሼር ማድረግ አይርሱ:: እናመሰግናለን::
Make sure to subscribe to Yehunie Belay Tube Channel and turn on notifications to stay updated
https://www.facebook.com/yehuniebelay...
https://www.instagram.com/yehuniebelay/
https://yehuniebelay.com
Any unauthorized use, copying or distribution is strictly prohibited.
Copyright ©2020:

የ7 ቤት አገው የፈረሰኞች በዓል ከ1932 ዓ/ም ጀምሮ በየዓመቱ በብሔረሰብ አስተዳደራችን በተለያዩ ወረዳዎች እየተዘዋወረ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ የሚገኝ የፈረሰኞች ባህላዊ በዓል ነው፡፡
የዚህ በዓል አጀማመር መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ፈረስ በአድዋ ጦርነት ወቅት ያደረገውን አስተዋጽዖና ይህም ታሪክ እንደገና የጣሊያን ፋሽስት ወራሪ ጦር አገራችንን በወረረበት ጊዜ ባደረገው የ5 ዓመታት የቅኝ ግዛት ሙከራ ጀግኖች አባቶች ጠላትን ድል ለማድረግ ፈረስና ፈረሰኞች ያደረጉትን የአርበኝነት ተጋድሎ ለማስታወስ፦
እንዲሁም ይህ በዓል በየዓመቱ ጥር 23 የሚከበርበት ምክንያት አርበኞች በዚሁ እለት በአድዋ ጠላትን ድል ያደረጉበት በመሆኑ የጊዮርጊስን ገድል ለማሰብ ጭምር ነው፡፡
ይህ በዓል ከቀበሌ እስከ ዞን አባቶች ባቆዩለት ባህላዊ አደረጃጀት መሰረት ማህበሩ ከ6 ሺ በላይ በሚደርሱ አመራሮች ራሱን በራሱ እየመራ ያለማንም ተጨማሪ አጋዥ በየዓመቱ ለአንድም ጊዜ ሳይቋረጥ እየተከበረ የመጣ በዓል ነው፡፡
ይህ ባህላዊ አደረጃጀት ከዛሬ 80 አመት ጀምሮ ያልተማከለ አስተዳደርን እውን ማድረግ የጀመረ፣ በየአራት አመቱ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ በማካሄድ የሚታወቅ፣ ከሃላፊነት ለሚወርዱ ሰዎች የአለቅነት ክብር በመስጠት የሚታወቅ፣ በሴቶች እኩልነት የሚያምን አንጋፋ ማህበር ነው፡፡
ይህ የፈረስ ማህበር ደስታን በማድመቅ፣ ሀዘንን በመጋራት፣ በባህላዊ መንገድ ፍትህን በመስጠት፣ ኃይማኖታዊ በዓላትን በማድመቅ፣ በህዝቡ ዘንድ ወንድማማችነትን በማጠናከር፣ የርስ በርስ መረዳዳትና መተሳሰብን በማጎልበት፣ ለቀጣዩ ትውልድ የአካባቢውና የብሄረሰብ አስተዳድሩን ብሎም የአገርን መልካም ገጽታ ለመገንባት እና ቅድመ አያቶች ያቆዩትን ታሪክ ለትውልድ ማስተላለፊያነት የሚያገለግል ታሪክን፣ ባህልንና ኃይማኖትን አቀናጅቶ የያዘ በዓልና ቅርስ ነው፡፡