ፍኖተ ሰላም ከተማ|Welcome to Finote Selam.2019 | መልካም ቆይታ ለኑሮ, ለፍቅር , ለኢንቨስትመንት ምቹ እዉነተ ሰላም ናት! #ፍኖተሰላም



Published
ETHIOPIA | Yehunie Belay | ፍኖተ ሰላም ከተማ | Welcome to Finote Selam. 2019
ይህ የይሁኔ በላይ የዩቲብ ቻናል ነው:: በየጊዜው ለሚለቀቁ ስራዎች በቀጥታ እንዲላክላችሁ ቻናሉን ሰብስክራይብ እና ሼር ማድረግ አይርሱ:: እናመሰግናለን::
Make sure to subscribe to Yehunie Belay Tube Channel and turn on notifications to stay updated
https://www.facebook.com/yehuniebelay...
https://www.instagram.com/yehuniebelay/
https://yehuniebelay.com

ፍኖተ ሰላም ከተማ የምትገኘው በሰሜን
ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በአማራ ብሔራዊ
ክልላዊ መንግሥት አስተዳድር ስር ነው።
ከተማዋ የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና
ከተማም ናት።
ፍኖተ ሰላም ከተማ በምዕራብ ጎጃም ዞን
ጃቢ ጠህናን ወረዳ ከአዲስ አበባ በ387
ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ እና ከክልሉ ዋና
ከተማ ከባህር ዳር ደግሞ 176 ኪሎ
ሜትር እርቀት ላይ ትገኛለች፡፡
አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋም በ10º
41’ ሰሜን ላቲቲውድ እና 37º 16’
ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው። ፍኖተ ሰላም
(ፍ/ሰላም) በኢትዮጵያ ውስጥ በጎጃም
እምብርት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት።
የከተማዋ አመሠራረት፦
ፍኖተ ሰላም ከተማ የተቆረቆረችው በ
1933 ዓ.ም ነው፡፡ፍኖተ ሰላም በክልሉ
ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንዷ ስትሆን
የከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት በ2003
ዓ.ም የተዘጋጀ መዋቅራዊ ፕላንም አላት፡፡
ፍኖተ ሰላም ማለት መልካም መንገድ
ወይም ጉዞ እንደማለት ሲሆን ይህንንም
ስም ያወጡላት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
እንደሆኑ ይነገራል። ጃንሆይ ከጣሊያን
ጦርነት በኋላ ከስደት ወደ ኢትዮጵያ
ሲመለሱ አሁን ፍኖተ ሰላም ያለችበት ቦታ
ላይ ከአጃቢዎቻቸው ጋር እረፍት ያደርጋሉ።
እስከዚያን ጊዜ ድረስ ያደረጉት ጉዞም
በሰላም የተሞላ ስለነበር ያንን ቦታ ፍኖተ
ሰላም ብለው ሰየሙት ይባላል።
ለዚህም ከከተማዋ ወጣ ብሎ የሚገኝ
አንድ የዋንዛ ዛፍ ይገኛል። ይህንንም
የዋንዛ ዛፍ የተከሉት ንጉሱ ስለነበሩ
እስካሁን ድረስ የአባ ንጉስ ዋንዛ እየተባለ
ይጠራል።
ፍኖተ ሰላም በብዙ ነገር ትታወቃለች
በአካባቢው ያሉ ገበሬዎች ጤፍ፣ በቆሎ፣
ዳጉሳ፣ ኑግ፣ በርበሬ እና ሌሎችንም
የእህል አይነቶች ይመረታሉ። በአትክልትና
በፍራፍሬ ልማት ደግሞ ሎሚ፣ ብርቱካን፣
ፓፓዬ እንደልብ ይገኛል። በጣም ጥራት
ያለው ቡና የሚገኝባት አካባቢም ናት
ፍኖተ ሰላም።
የባከል ቡና በጣዕሙ ይታወቃል።
ከከተማው ወጣ ብሎ የገራይ የውሃ
ግድብ ስለሚገኝ በተለይ በፆም ጊዜ እጅ
የሚያስቆረጥም አሳ ይገኛል።
ፍኖተሰላም በወተትና በማር ሀብት በጣም
የታወቀች ከተማ ናት። በከተማዋ ሁለት
መለስተኛ የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል
ት/ቤት፣ ሁለት ሁለተኛ ደረጃ ፣ አንድ
ከፍተኛ ትምህርት መሠናዶ ት/ቤት፣አንድ
የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣አንድ ጤና
ጣቢያ፣አንዲሁም አንድ መምህራን
ትምህርት ኮለጅ እና አንድ ቴክኒክና ሙያ
ኮሌጅ ይገኛሉ።
በመሆኑም ፍኖተሰላም ዩኒቨርስቲ
ባለመኖሩ በርካታ ኢኮኖሚያዊና
ማህበራዊ ልማቶችን አጥታለች።ትንሹ
ማሳያ የምዕራብ ጎጃም ዞን ወረዳዎች
ፍኖተሰላምን ጨምሮ የኮቪድ-19
ላቮራቶሪ ምርመራ የሚደረገው ወደ
እንጅባራ ዩኒቨርስቲ አልያም ወደ ባህርዳር
ተልኮ ነው ውጤት የሚታወቀው።ሌላም
ሌላም------
በማርልኝ ም ስ ክ ር