ጣይቱ የባህልና የትምህርት ማዕከል የ 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል!



Published
ጣይቱ የባህልና የትምህርት ማዕከል የ 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል!
Tayitu official website
https://www.tayitu.org/
You can donate with your credit/debit card or PayPal
****************
Tayitu Cash App
$Tayitu
*****************
Tayitu Venmo
@Tayitu
*****************
Tayitu official YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCNIDC3wGHS-c2GiK8gLTu-Q
SUBSCRIBE SHARE LIKE
**************
For more info
Tayitu Center Phone
(800)-375-7592
ኢትዮጵያ ትልቅነቷን የሚመሰክሩ ታሪካዊ ሥፍራዎች የባሕል እሴቶች የተለያዩ የጥበብ ዘርፎች አሏት:: የተለያዩ ብሔረሰቦቿ በየቋንቋቸው በአኗኗር ዘይቤአቸው በወግ ዕቃዎቻቸው የሚያመለክቱት የረጅም ጊዜ ቅርስና ቶፊቶችን ያመለክታሉ:: ይህንን መሠረት በማድረግ ጣይቱ የባህልና የትምህርት ማዕከል በሰሜን አሜሪካ በሐምሌ ወር በ2000 ዓመተ ምህረት ከትርፍ ነፃ ሆኖ ተመሰረተ:: ይህ ድርጅት ባለፉት 20 ዓመታት በስደት ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን ባሕልና ታሪክ በማስተዋወቅ በመላው ሰሜን አሜሪካ -በካናዳ -በአውስትራሊያና በአውሮፓ ሲዘዋወርና ሊታሰብ የማይቻሉ የጥበብ ሥራዎችን አቅርቧል:: በሥነፅሑፍ - በቴአትር - በትምህርትና በማዕከል ምስረታ ትልቅ ሚና ተጫውቷል:: ቋሚ በጀት ሳይኖር ቋሚ ሰራተኞች በሌሉበት የተከናወኑት ተግባራት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚያኮራ ነው:: በአጠቃላይ :
239 የግጥም ምሽቶች ያካሄደ ሲሆን 3554 ወጣትና አንጋፋ ፀሐፊያን ተሳትፈውበታል:: እውቅ 67 እንግዶችን ጋብዞ ያስተናገደና ቴአትርን በተመለከተ 64 የትወና ሥራዎችን አቅርቧል:: ከ182 ተዋንያን ውስጥ 71ፕሮፌሽናል ሲሆኑ 111 በድርጅቱ የሰለጠኑ አማተር ተዋንያን ናቸው:: 389 ትርኢቶችን በ285 የቴአትር ጉዞዎች አሳይቷል:: 18 የተለያዩ workshops የተደረጉ ሲሆን እነሱም በትወና / በቋንቋ በፊልም ዝግጅት / በገፅ-ቅብ /በመገናኛ ብዙኃን/ በማህበራዊ ድህረገፅና -በመሳሰሉት ነው::
በትዳር ዓለም ከ40-50 በጋብቻ ለቆዩት ቤተሰቦች እውቅና በመስጠት የማህበራዊ ኑሮን ሲያጠናክር ቆይቷል::
ዓመታዊ የአፍሪካ የግጥም ምሽት እንዲሁም ደግሞ " ጣይቱ በኢትዮጵያ" በሚል ወጣት ገጣሚያንን በማበረታታት በሥነ ፅሑፍ መስክ ከፍተኛ አመርቂ ስራዎችን አከናውኗል:: የመጀሙሪያውን የአማርኛ ቤተመፃሕፍት በዋሽንግተን ከመክፈቱም በተጨማሪ መሰል ማህበራትን በየሥፍራው እንዲመሰረቱ አግዟል:: በዚህና በመሳሰሉት የሃያ ዓመታት አኩሪ ተግባራት ከ54 በላይ የሚሆኑ ሽልማቶችንና የምስጋና ወረቀቶችን ከከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎችና ሕዝባዊ ድርጅቶች ተቀብሏል::
እነሆ ይህንን የከፍተኛ ውጤቶቹን በዓል በድምቀት ለማክበር ሁኔታዎች ባለመፍቀዳቸው ፕሮግራሙን በZOOM በ YouTube በፌስቡክ ለማካሄድ ተገዷል:: አብረውን በውጣ ውረዱ ወቅት ለትጏዙት የድርጅታችን ደጋፊዎች አድናቂዎችና አባላቱ በሙሉ ከፍተኛ ምስጋና እያቀረብን አሁንም ያለእናንተ እርዳታና ድጋፍ መንቀሳቀስ ስለሚያዳግተን በፕሮግራሙ እንድትሳተፉና አብራችሁን እንድታከብሩ እንጠይቃለን::