Nhatty Man - Wetat - ናቲ ማን - ወጣት [New Ethiopian Music 2023]



Published
አልበሙን በመግዛት ድጋፎን ማሳየት ከፈለጉ
https://realnhattyman.bandcamp.com/album/vol-4

Supported by the Australian Government through the Australia Council for the Arts, its arts funding and advisory body.

፪ ወጣት
ተሳስረን ቆመናል ካለንበት
ከዘፈቀን ላንወጣበት
የማልን ይመስል ቃል ያለን
ዛሬም እዚያው ላይ ነን
ተፎካክረን ተናንቀን ተራርቀን
መላ እንዳጣ ተለያይተን

የ አውቅልሃለው ባይ የቅቤ አንጏች ዜማ
ህይወት እየቀማ
የስንቱን ጎበዝ ትልም ያጨለመው
ዛሬም በዚኅ ዘመን መቶ ሳየው
እንዴት ዝም እላለሁ እኔ

ውቢት ይኅን ዜማ ሳዘጋጀው
ላንቺ ነበር ውበትሽን አመልሽን በዘመንሽ ምት ላሞግሰው
ግን ምን ያደርጋል ሀገር ከሌለች አንችም የለሽ እኔም የለው
ማጌጥ መዋባችንም ከንቱ ነው

የሁላችንም ሃሳብ እንደተራራቀ አለ
ተስፋን እየጣለ ክፋት እያየለ
ግን ወጣት ሀገርህ ያንተው ናት
ያዝ

ልብህ እንደፈቀደ እንዳሻ ምት ሆንባት
ዛሬም እልሃለሁ ሀገርህ ቤጥ ናት
በቋንቋ እየመረጡ ስያሜ እየሰጧት
ለያይተው በታትነው ባንተ ዘመን ላይ ጣሏት
ከ ፵ ከ ፶ ከ ፷ ዓመት በላይ
ሀገሬ አልዳነች ከዚኽ አዙሪት ከዚኽ ስቃይ
ይልቅ ለዘር መደረብን ተውና
ተሸነፍ ለፍቅር ጀግንና
ዘመንህን ምሰል እንደወቅትህ
እንደ ወጣትነትህ
ሁሉን እንደቸረህ በነጻ
እንደ ቃሉ ሁሉን ውደድ ልብህ ይንጻ
ስተትን ማይደግም ብለህ ነው
ባለፈ የተማረው

ወጣት ወጣት
አለው በል ንቃ ሀገር ያንተው ናት

በታላላቆቻችን ስህተት ብዙ ዋጋ ከፍለናል
ከምትወደው ከሚወዳት ስንቱ ሲነጥል አይተናል
ካደገበት ከቀዬው
ከጎረቤት ሲለያይ አየከፋው

ከ አሁን አሁን አብሮነታችን ይታደሳል ስንል
የ እናት እንባ ይታበሳል ስንል
እንዴት እንበታተን
እንዴት እንጨካከን (እኛ)

ውጣ ከሰፈር ግዘፍ ለሀገር
እንደቀደሙት ዝናህ ይነገር
እንዲህ ነው ብለው በሰየሙህ
እንዲ ነኝ አትበል አጥር ሰርተህ
ይቅር መጠላላት ይቅር መጠላለፍ
ቂም ቦታ ይጣ ያለን እናትርፍ
ክፉ አታልምደው ንጹ ልብህን
ብዛ ለብዙ እወቅ ያለህን

ወጣት ወጣት
አለው በል ንቃ ሀገር ያንተው ናት