Nhatty Man - She Gize ናቲ ማን - ሺ ጊዜ - New Ethiopian Music 2023 - አዲስ አልበም 2023 [New Album 2023]



Published
አልበሙን በመግዛት ድጋፎን ማሳየት ከፈለጉ
You can buy the album on
https://realnhattyman.bandcamp.com/album/vol-4

Supported by the Australian Government through the Australia Council for the Arts, its arts funding and advisory body.

፭ ሺ ጊዜ
ሳይሽ መራዴ
ሳጣሽ በሐሳብ መንጎዴ
የወደደ አመሉ ይሄ አይደለም ‘እንዴ
ትንሹም ትልቁም በልቡ ያለውን
ፍቅር አይደለም ወይ
የሚገልጠው ጠባዩን

ተጋኖ ተካብዶ ሚነገር
መውደዴ የኔ አንቺን ማፍቀር
አይገርመኝ ባንቺስ የምባለው
ወድጄሽ ሰላም ያተረፍኩት እኔው
የህይወቴን ምዕራፍ
ያኔ እና ዘንድሮን
ልዳኘው ራሴው
ያየሁት መልካሙን
እንኳን ለፍቅርና ላሳረፈው ቀርቶ
ስንቱ ልቡን ይጥላል ባመነበት ፀንቶ

ሺ ጊዜ
በ አንቺ እኔ
ልታማ ባንቺ ስያሜ ይውጣልኝ
ቀልቡ ጠፋ ቀልብ ራቀው
አንቺን ወዶ እሷን ወዶ

ቀልቡ ጠፍቷል የሚሉኝ ምነው
ባፈቀረው ላይ አርፎልኝ ነው
ቀልቡ ጠፍቷል የሚሉኝ ምነው
በወደደው ላይ አርፎልኝ ነው
ልቤ ሰክኖ ተረጋግቶ
ፍቅርን አይቶ
እሷን ወዶ