Nhatty Man - Amelwa - ናቲ ማን - አመልዋ - [New Album 2023] አዲስ አልበም 2023



Published
አልበሙን በመግዛት ድጋፎን ማሳየት ከፈለጉ
You can buy the album on
https://realnhattyman.bandcamp.com/album/vol-4

Supported by the Australian Government through the Australia Council for the Arts, its arts funding and advisory body.

፮ አመልዋ
እሷም እኔን መስላለች እኔም እሷን እሷን
ፈቅዶ ነው ያላመደን ፍቅር ያጣመረን
ፀባይዋን አመሏን እንደ ህልሜ አድርጎት
የምኞቴን ሰው ባገኝ የልቤን ፍላጎት
ትሁን ትዘዝ ብዬ በላዬ ላይ ሾምኳት
እንደቃሏ ልገኝ በኪዳን አሰርኳት

ለሷ ብቻ ቢያደላ እውነት አለው ልቤ
ሆና ተገኝታ ነው እንደሃሳቤ
ለወደደው ቢያደላ እውነት አለው ልቤ
ሆና ተገኝታ ነው እንደሃሳቤ

ወርቅ አምሏ ገዝቶኝ
ጥሩነቷ ማርኮ
እርም ሌላ ያስማለ
ለኔ የገብኝ ሀቅ አለ

ግርማውን ሳቢ ውበቱን
ሸጋ አመል የሴትነቱን
በልኩ አጎናጽፏት
ነገር ሁሉ ሲያምርላት
ለሃሰት ጽዩፍ ምላሷ
ቅጥፍት አታውቅም እሷ
ደሞ በዚህ ዘመን
የለም ሲሉ ሚታመን

ከቀረብኩት ሁሉ እሷን ቢለያት
የባከነው ቀልቤ ሰከነላት
አንደበቴ ስሟን የሚያሞካሸው
ህይወቴ አምሮ ነው
ህይወቴ አምሮ ነው

ለሷ ብቻ ቢያደላ እውነት አለው ልቤ
ሆና ተገኝታ ነው እንደሃሳቤ
ለወደደው ቢያደላ እውነት አለው ልቤ
ሆና ተገኝታ ነው እንደሃሳቤ

አምኜ ብወዳት
ሞልቶ ነው ጎኔ
አምሮ ህይወቴ