Nhatty Man - Abaree - ናቲ ማን - አባሪ [New Album 2023]



Published
አልበሙን በመግዛት ድጋፎን ማሳየት ከፈለጉ
You can buy the album on
https://realnhattyman.bandcamp.com/album/vol-4

Supported by the Australian Government through the Australia Council for the Arts, its arts funding and advisory body.

፫ አባሪ

መች ይጠፋል በደግ ቀን አባሪ
መች ይጠፋል በብራ ቀን አባሪ
ስያሜው የሚገባው እውነተኛ አፍቃሪ
ያንቺ አይነት ሲሆን ነው በክፉ ተጠሪ

አለሁ አለሁ የሚልህ ሁላ ስትፈልገው የለም.
ሰው ባሻህም ጊዜ ቀድሞ አልተገኘም
በቃ ቁረጥለኝ ሁሉን አትመን ብዬ
ልቤን እንዳልሞግት ረታሺኝ አንቺዬ

ባንቺ የተማርኩት እውነት
ሰው መውደድ ንጹህ ማንነት
ደሞ ቅን ልብሽ የፍቅር ስጦታሽ
ማረከኝ እንዳምንሽ

መች ይጠፋል በደግ ቀን አባሪ
ስያሜው የሚገባው እውነተኛ አፍቃሪ
ያንቺ አይነት ሲሆን ነው በክፉ ተጠሪ

ደግሜ ላሞካሽሽ ደግሜ
የእውነት መውደድን ካንቺው ቀስሜ
ተከቦ ተደንቆ መኖርን ባውቅም
ለክፉ ደራሽ ገጥሞኝ አያውቅም
ድሮ ድሮ ካንቺ በፊት
ይመስለኝ ነበር ሰው ሁሉ አንድ አይነት
ፍቅርን አውቆ ተቀይሮ
ልቤ በጥፍ ወደደሽ ጨመሮ
ከሰማሁት ካየሁትም በላይ
ትለያለሽ ስል አልሆንም አባይ
አምና ሸለመቺኝ ፍቅሯን
ታምና አሳየቺኝ ልቧን
በከተማው ሺ ቆንጆ በሞላበት
ውበት አይነ አዋጅ በሆነበት
ቢፈለግ ጠፍቷል ለኔ እንዳንቺ አይነት